4ተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ሲምፖዚየም በዩኒቨርሲቲያችን ተካሂዷል

Share this story

Posted on: Jul 19,2018

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያዝያ 26 እስከ 27/2010 ዓ.ም የተካሄደው አገር አቀፍ የምርምር ሲምፖዚየም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለአገር ልማትና ዕድገት የሚኖራቸው ጠቀሜታ የጎላ መሆን እንዳለበት ተጠቆሟል፡፡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከመላው የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ስራዎቻቸውን በሁለት ቀናት ያቀርቡ ምሁራን አራተኛውን አገሯዊ የምርምር ጉባኤ አጠናቋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በሲምፖዚየሙ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በምሁራን የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች አገራዊ እድገትና በህዝቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ መሆን አለባቸው፡፡ በእዚህ በኩል ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉ ምህራኖች የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በመስራት ለፖሊሲ አውጪ አካላት ግብአት የሚሆኑ በርካታ የጥናቶች ውጤቶች አስተዋጽኦ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በምርምር ሲምፖዚየም የተለያዩ የምርምር ሥራዎች ቀርበው በምሁራን ውይይት ተደርጓል። የመድረኩ ተሳታፈዎችም በቀጣይ የምርምር ሥራዎቹ ወደ ተግባር ተቀይረው የማህብረሰቡንና የሀገር ችግር ፈቺ በሚሆኑበት ጉዳይ ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በምርምር ጉባኤው ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ የተሳተፉት ፕሮፈሰር አፈወርቅ ካሱ እንዳሉት ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በአገራችን ካሉት 10 የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱና

የኢንዱስትሪ ኮርደር በሆነችው ድሬዳዋ ከተማ መቋቋሙ ዩኒቨርሲቲውን ልዩ እንደሚያደርገው በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

በምሁራን የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች በእነዚህና መሰል የልማት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርጉ እን ደሚገባም አመል ክተዋል። ምሁራን የከተሞች መስፋፋት፣ ዓለም አቀፍን መሰረት ያደረገ የዕውቀት ውድድር፣ የ ህ ዝብ ቁጥር መጨመር ለሀገር ልማትና ዕድገት ፈተና እንደሚሆኑ አውቀው በመፍትሄው ላይ አተኩረው ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲተጋባዥ ፕ/ር ጠናለም አየነው በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄደ ባለው የምርምር ጉባኤ ጠቃሚ ልምዶችን እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል የሆኑት ክቡር አቶ ኢብርሂም ኡስማን በምርምርና ጥናት ወርክሾፕ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ እድገት ለመረዳትና የሚደረገው የዕውቀት ሽግግር ለትምህርትና ስልጠና ስራዎች እንደ አቅም ማጎልበቻ መጠቀም አለባችሁ ብለዋል፡፡

የጉባኤው መካሄድ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በቀጣይ ለሚያደርጉት የጥናትና ምርምር ሥራዎች ልምድና አቅም እንደሚሆን እና ይህ ስምፖዚየም መካሄዱ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በ2010 በጀት አመት ሚያዝያ 26 እና 27/2010 ዓ.ም በአራተኛዉ አገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በድሬዳዋ ዩኒቨርሰቲ “Research for Socioeconomic Transformation and Sustainable Development ”በሚል መሪ ቃል በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ ይሄዉም በወርክሾፑ በኩል call for paper ጥሪ ተደርጎ 343 አብስትራክት ተልከዉ የምርምር ካዉንስሉ ባወጣዉ መስፈርት መሰረት በሁለት ደረጃ መረጣ ተካሂዶ 36ቱን በመምረጥና አስፈላጊ ዝግጅቶችን በማከናወን በኮንፈረንሱ ላይ እንዲቀርቡ መደረጉን የምርምርና ቴክኖሎጂ ልውውጥ ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ሊበን ገልጻል፡፡

የተመረጡት የጥናቶቹ ባለቤት ሁሉ ኮንፍረነሱ ላይ እንደሚቀርቡ ከገለጹ ቦኋላ 2ቱ በተለያየ ምከንያት አላቀረቡም፡፡ 36ቱ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የምርምር ስራቸዉን መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተጋበዙዥ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አቅርበዋል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት የመጡ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ከላይ የተገለጸዉ የኮንፈረንሱ መሪ ቃል የተመረጠበት ምክንያትም አሁን ሀአገራችን ከያዘችው ዘላቂ የሆነ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ/GTP2 ጋር የሚጣጣም በመሆኑ ነዉ፡፡ እንደዚሁም ዘላቂ እድገት እዉን የሚሆነዉ በሳይንቲፊክ ምርምር ሲመራና ለዚህም የምሁራን ሚና ሁለንተናዊ ለሆነ የአገር እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ ለማሰገንዘብ ነዉ፡፡

መሪ ቃሉ ለተመራማሪዎች የወቅቱ የምርምር ስራ ትኩረት ቴክኖሎጂን በማፍለቅ/ በመቅዳትና በመጠቀም ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ መልእክት ያሰተላልፋል፡፡

ኮንፍራንሱን በያዝነዉ አመት ለየት ያደርገዉና ድምቀት የሰጠዉ የሀገራችን ሁለት ተዋቂ ፕሮፌሰሮች መጋበዛቸዉ ነው፡፡ እነሱም ክቡር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ - የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ እና ፕ/ር ጠናአለም አየነዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የበለስ ኢንጂነሪንግ (PLC) ማናጀር ማኔጀር ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት የሀገራችን ምሁራን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ በተገኙበት ለታዳሚዉ key-note speech አቅርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

ኮንፍረንሱም ሁለት አይነት አቀራረቦች ነበሩት፡፡ የመጀመሪዉ plenary ses-sion ሲሆን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግሮች፣ የመክፈቻ ንግግሮችና key-note addresses የቀረቡበት ነዉ፡፡ .

ሁለተኛዉ Parallel session ሲሆን ጥናቶቹ በሶስት ድሲፕሊን ተከፈሎ ነበር የተካሄደው፡፡ የመጀመሪያው አፕላይድ ሳይንስና ግብርና ነክ፣ ሁለተኛው ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ሶስተኛው ሶሻል ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ እና ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ናቸው፡፡