ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 11ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተከበረ

Share this story

Posted on: Dec 06,2016

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች 11ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህዳር 25 እና 26/2009 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ አክበረውታል፡፡

ህዳር 25/2009 ዓ.ም በተደረገው አከባበር ላይ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለበአሉ ትልቅ ድምቀት ሰጥተውት ነበር፡፡ ተማሪዎቹ የመጡበትን ክልልና ብሔረሰባቸውን በመወከል በዩኒቨርሲቲው ስቴድየም ደማቅ ሕብረ-ብሔራዊ ትዕይንት አሳይተዋል፡፡ “ብዝሃነታችን ውበታችን” የሚለውን በአደባባይ አስመስክረው ውለዋል፡፡

በእለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት በአሉን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዳር 26/2009 ዓ.ም 11ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይትና በኢፌድሪ ህገመንግስት ዙሪያ የጥያቄ ውድድር በማካሄድ በዓሉ ለሁለተኛ ቀን ተከብሮ ውሏል፡፡