የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮች ተብለው የተቀመጡትን ጉዳዮች አካቶ ከመስራት አንፃር የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ጽ/ቤት በ 2003 አ.ም ተቁቁሞ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኘል፡፡ ስርአተ ፆታና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ በክፍሉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰሩባቸው ካሉ ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው፡፡

የክፍሉ ራእይ

የስርዓተ ጾታ እኩልነት የሰፈነበት ተቋም መፍጠር

የክፍሉ ተልእኮ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች በማህበራዊ፣ ምጣኒ ሃብታዊና በፖለቲካው መስክ እኩል ተሳታፊ የሚሆኑባት የትምህርት ተቋም እንዲሆን ተልእኮ አለው

እሴቶች

 • የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ
 • ተቋሙ ለሴቶች ምቹ የትምህርትና የስራ አካባቢ እንዲሆን ማድረግ
 • ሴቶች የአመራር ድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ( ማብቃት)
 • በሴትና በወንድ ተማሪዎች መካከል ያለው የትምህርት ተሳትፎ ክፍተት እንዲጠብ ማድረግ
 • ጠንካራና ብቁ ተወዳዳሪ ሴት ተማሪዎችን ማፍራት
 • የስርዓተ ጾታ ግንዛቤን ማስፋት
 • ጾታዊ ትንኮሳን ማስወገድ እና ተፈፅሞም ሲገኝ ተገቢው ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ
 • ሙስናን መዋጋት ፍትሃዊነትና አለማዳላት
 • ከስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ነፃ የሆነ ተማሪ ማፍራት

የክፍሉ ዓላማና ግብ

ዓላማ

ክፍሉ ለ 2006 ዓ/ም እንዲተገበር ያወጣውን እቅድ መሰረት በማድረግና የአሰራር ስርዓት አቅጣጫ በመከተል የዩኒቨርሲቲው ራእይ እንዲሳካ ማድረግ ፣ የስርዓተ ጾታ እኩልነት የሰፈነበት ተቋም እንዲሆን በማድረግ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደር ማስፈን በሚያስችል ተቋማዊ ሽግግር የተቋሙን ራእይ ማሳካት፡፡

ግብ

 • ሴት ተማሪዎች በትምህርታው ጠንካራ ተወዳዳሪ ይሆናሉ፡፡
 • የሴት ተማሪዎች የትምህርት ማቋረጥና መባረር ይቀንሳል ብሎም ይጠፋል
 • ዩኒቨርሲቲው ለሴቶች ምቹ የትምህርትና የስራ አካባቢ ይሆናል፡፡
 • የሴቶች በራስ መተማመን ይጨምራል
 • ጾታዊ ትንኮሳ ይወገዳል
 • የስርዓተ ጾታ እኩልነት ይሰፍናል

የክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት

 • የጾታ እኩልነት እንዲረጋገጥ ማስቻል
 • የሴት ተማሪዎች የአካዳሚክ አቅማቸው እንዲጎለብት ማድረግ
 • ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ማስቆም
 • ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍና እገዛ በማድረግ በአካዳሚክ አቅም አጎልብተው ለአገር ልማትና እድገት እንዲበቁ ማስቻል
 • ሴቶችን ለአመራር ማብቃት
 • የስርዓተ ጾታ ግንዛቤን ማስፋት
 • የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ (ተማሪዎች በተለይ) በቂ የስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ
 • ተማሪዎችን ወደ ብልሹ ስነ ምግባር የሚመሩ ምክንያቶችን በመለየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መፍትሄ ማፈላለግ
 • በአጠቃላ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በዩኒቨርሲቲው እቅድ ውስጥ ተካተው መሰራታቸውን መከታተልና ማሰተባበር