የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በ1999 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ተብለው በተለዩ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በተለይም በ2002 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ፅ/ቤት በማቋቋም ሴት ተማሪዎች በማናቸውም ዘርፍ ከወንድ አቻዎቻቸው እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻልና ሴቶች በውስጣቸው ያለውንንና በተለያዩ ተፈጥሯዊ ባልሆኑ ምክንያቶች ሊጠቀሙባቸው ያልቻሏቸውን ክህሎቶች እንዲያወጡ ምቹ የመማርና የማስተማር አካባቢን በመፍጠር ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡