የምርምርና ቴክኖሎጂ ልውውጥ ዳይሬክቶሬት ለሲኒየር መምህራን የጥናትና የምርምር ስራዎችን በማዘጋጀትና በማሳተም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ልውውጥ ዳይሬክቶሬት ለዩኒቨርሲቲው መምህራን በጥናትና ምርምር ሲኒየር በሆኑ ምሁራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመምህራኖቻችን እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ለአብነትም በ2009 ዓ.ም ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ፕሮፈሰር ፈቲህ አባዲ እና ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር አቢ ታደሰ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ይታወሳል  ዳይሬክቶሬቱ አሁንም የዩኒቨርሲቲያችንን መምህራን የምርምርና ጥናት ስራዎችን በታወቁ ጆርናሎች ላይ በቀላሉ እንዴት ማሳተም እንደሚቻል የክህሎት ስልጠና እንዲዘጋጅ አድርጓል፡፡

በእዚህም መጋቢት 14 እስከ 15/2010 ዓ.ም ለሲኒየር መምህራን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

ሲኒየሪ ተመራማሪ በሆኑት በፕሮፈሰር ፍቃዱ በየነ የምርምርና የጥናት ስራዎችን ለህትመት እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸውና በምን መልክ ማሳተም እንደሚችሉ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ፕሮፈሰር ፍቃዱ አንድ የምርምርና ጥናት ስራ በአለም አቀፍ ጆርናሎች ተቀባይነት እንዲኖረው ማካተት ያለበት ንዑስ ርዕሰ ጉዳይና ይዘት ምን መምሰል እንዳለበትና ተመራማሪዎቹ ሊከተሉ የሚገባቸው የምርምር ስነ-ምግባር፣ ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ከርዕስ አመራረጥ እስከ ህትመት ድረስ ያለውን የስራ ሂደት በስፋትና በጥልቀት በስልጠናው አካታው አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ

አንዳንድ ጆርናሎች ገቢን ማዕከል አድረገው የተመሰረቱና የሚያሳትሟቸው የምርምር ስራዎች ብቃትና ጥራት የሌላቸው እንደሆኑ በመግለጽ ሠላጣኞቹም እነዚህ አለም አቀፍ እውቅና ለሌላቸው (Predatory) ጆርናሎች ስራቸውን ከመላካቸው በፊት ማጣራት እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ ቀናት ዳይሬክቶሬቱ ለሴት ተመራማሪ መምህራን በጥናትና ምርምር አሠራር እንዲሁም በፕሮፖዛል አዘገጃጀት ዙሪያ የ4 ቀናት ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲኒየር ተመራማሪ በሆኑት በዶ/ር አስቴር ፀጋዬ ሰልጠና እንዲያገኙ አደረጓል፡፡ በእዘህ ስልጠና የዩኒቨርሲቲያችን ሴት መምህራን ለቀጣይ የምርምር ስራቸው በቂ ግንዛቤና ዕውቀት እንዳገኙ መረዳት ችለናል፡፡